
በመጪው የኦገስት ወር ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እየተጠናከሩ ሊሄዱ እንደሚችሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በፀሐይ ሀይል ታግዘዉ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በመነሳት በረዶ የቀላቀለ እና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡