1-31 August 2024

Bulletin

በመጪው የኦገስት ወር ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እየተጠናከሩ ሊሄዱ እንደሚችሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡