1-30_September 2024

Bulletin

በመጪው ሴፕቴምበር በምዕራብ አማራ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ፤ በኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፤ በመጠን ረገድ ደግሞ አብዛኛው ትግራይ፤ የአማራ ምሥራቃዊ አጋማሽ፤ በመካከለኛው ኦሮሚያ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎችን ጨምሮ ከመደበኛው በላይና መደበኛ ዝናብ እንደሚኖር የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ በረዶ የቀላቀለና ነጎድጓድ አዘል ከባድ ዝናብ በተለይ እስከ ወሩ አጋማሽ ድረስ ይኖራቸዋል።