
በመጪው የጁን ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የአሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተለይም በምዕራብ አጋማሽ ኢትዮጵያ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩ ደመናዎች ላይ በመነሳት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ