1-30 September 2026

Bulletin

በመጪው ሴፕቴምበር በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ፤ የኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፤ በመጠን ረገድ ደግሞ አብዛኛው የምዕራብ ትግራይ፤ የአማራ ምሥራቃዊ አጋማሽ፤ የመካከለኛው ኦሮሚያ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎችን ጨምሮ ከመደበኛዉ ጋር የተቀራረበ እና በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ከመደበኛው በታች ዝናብ እንደሚኖር የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ በተለይ እስከ ወሩ አጋማሽ ድረስ ይኖራቸዋል።