1-30 September 2025

Bulletin

በመጪው ሴፕቴምበር በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፤ ጋምቤላ፤ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ፤ ኦሮሚያ ምዕራባዊ አጋማሽ ላይ የክረምቱ ዝናብ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፤ በመጠን ረገድ ደግሞ አብዛኛው ትግራይ፤ የአማራ ምሥራቃዊ አጋማሽ፤ በመካከለኛው ኦሮሚያ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎችን ጨምሮ መደበኛና ከመደበኛው በላይ ዝናብ እንደሚኖር የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አልፎ አልፎ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ በተለይ እስከ ወሩ አጋማሽ ድረስ ይኖራቸዋል።