1-30 November 2026

Bulletin

በሚቀጥለው የኖቬምበር ወር ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከመጀመሪያዉ ሳምንት ጀምሮ በአንፃራዊ ሁኔታ እየተሻሻሉ እንደሚሄድና እስከ ወሩ መጨረሻ ደረስ ቀጣይነት የሚኖራቸዉ ሲሆን፣ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና፣ የምስራቅ ቦረና፣ የምዕራብ ጉጂ፣ ጉጂ እና የምስራቅ ባሌ ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ቀጣይነት ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡