በሚቀጥለው የኖቬምበር ወር ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እስከ ወሩ አጋማሽ ደረስ ቀጣይነት እንደሚኖራቸዉና ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በተለይም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረና የምስራቅ ቦረና፣ የምዕራብ ጉጂ እና ጉጂ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡባዊ ዞኖች ላይ ቀጣይነት ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡