1-30 June 2026

Bulletin

በመጪው የጁን ወር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ላይ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናቶች ላይ አንጻራዊ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛዉና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩ ደመናዎች ላይ በመነሳት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራቸዋል