1-28 _ February 2025

Bulletin

በመጪው ፌብርዋሪ ወር የበልግ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ እና ለዝናብ መኖር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከእዚሁ ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምሥራቅ፣ በምሥራቅ፣ በመካከለኛውና አጎራባች የስምጥ ሸለቆ ሥፍራዎች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡