1-20 February 2026

Bulletin

በመጪው የፌብርዋሪ ወር የበልግ ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ እንደሚሄዱ እና ለዝናብ መኖር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምሥራቅ፣ በምሥራቅ፣ በመካከለኛውና አጎራባች የስምጥ ሸለቆ ሥፍራዎች ላይ ከወሩ አጋማሽ በኋለ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡