
በሚቀጥሉት የኦገስትና የሴፕቴምበር ወራት ከአትላንቲክና ከህንድ ውቅያኖስ የሚገባው እርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ በተለይም በሰሜንና በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት የተሻለ ሆኖ ሊቀጥል እንደሚችል ከመጠበቁም በላይ በኦገስት ወር በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በፀሐይ ሀይል ተጠናክረው ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ አልፎ አልፎ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሴፕቴምበር ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች የፀሀይን አቅጣጫ ተከትለው ወደ ደቡብ ማፈግፈግ ስለሚጀምሩ በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ዝናብ ቀስ በቀስ መጣል ይጀምራል፡፡