
በሚቀጥሉት ሁለት ወራት (ኦገስት እና ሴፕቴምበር) በአብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተጠናከረ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ባሉት ቀናት በፀሀይ ሀይል ታግዘው ከሚፈጠሩ ጠንካራ ደመናዎች ቅጽበታዊ ጎርፍና የወንዞች ሙላት ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሊዘወተር ይችላል፡፡ የክረምቱ አወጣጥም በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብና መካከለኛወ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚዘገይ ሲሆን ከአብዛኛው የክረምት ዝናብ ተጠቃሚዎች ላይ ደግሞ መደበኛ ፈሩን ተከትሎ እንደሚወጣ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡