Mid Kiremt 2026
በቀጣዮቹ ሁለት የክረምት ወራት (ከኦገሰት እስከ ሴፕቴምበር 2026)፣ ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት እየተጠናከሩ ሊሄዱ እንደሚችሉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን፣ መካከለኛዉ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡