የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጉበኙ፡፡

አውደ-ርዕይ

01 Nov, 2023 Press Release

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ አውደ ርዕይን ጥቅምት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጉብኝተዋል፡፡

ጎብኝዎቹ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች ያሏትን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብት በአውደ ርዕዩ ላይ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልፀው መንግስት እነዚህን የቱሪዝም መስቦችንና መዳረሻዎችን በማልማት ረገድ ያለው ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አውደ ርዕዩ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ተከፍቶ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ሲሆን እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Tags: አውደ-ርዕይ