የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በጋምቤላ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ያስገነባው የG+2 ህንፃ አስመረቀ

05 Jan, 2025 News

photo_2025-01-05_03-54-48

ኢንስቲትዩቱ በጋምቤላ ክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ያስገነባውን የG+2 ህንፃ የጋምቤላ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም አስመረቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኢንስቲትዩቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሚቲዎሮሎጂ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ አስራ አንድ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከላትን በማቋቋምና አቅማቸውን በማሳደግ ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የጋምቤላ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ጋልትዋክ ሮን የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት በአየር መዛባት ሳቢያ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከለወ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የመሰረታዊ የሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም ስለ ህንፃው አጠቃላይ ማብራሪያ በመስጠት የምረቃ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡