የአየር ጠባይ መረጃና አገልግሎቶች ለEACEnhancing Adaptive Capacity to community ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ስልጠና ተሰጠ

25 Oct, 2024 News

photo_2024-10-25_23-01-11

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለEAC /Enhancing Adaptive Capacity to community/ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች በአየር ጠባይ መረጃና አገልግሎቶች ላይ ሥልጠና ተሰጠ፡፡ ሥልጠናው በምስራቅና መካከለኛው ኦሮሚያ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከል የተሰጠ ሲሆን በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት በአካባቢ ጥበቃ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ወ/የስ ሲሆኑ በሚቲዎሮሎጂ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በሚገኝበት በዚህ መድረክ ለመካፈል እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የመሰረታዊ የሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ በEAC ፕሮጀክት በአካባቢ ጥበቃ ባለቤትነት የሚመራ ሲሆን ለአርባ አንድ ቀበሌዎችና ሃያ ሁለት ወረዳዎች ላይ የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ መለሰ ለማ ስለፕሮጀክቱና ስለስልጠናው አጠቃላይ አላማና ያብራሩ ሲሆን በእለቱ ስድስት ፅሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡