የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀ-ግብር ላይ ተሳተፉ

23 Aug, 2024 News

photo_2024-08-23_15-54-10

ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም( ኢ ሚ ኢ ) "የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ !" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገር አቀፍ መርሀ-ግብር ላይ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ ወሬርሶ ማሊና ቀበሌ በሚገኝ የተራቆተ ተራራማ አካባቢ ሃያ ሰባት ሺ ችግኞችን ከውሃና ኢነርጂ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ጋር በመሆን ተክለዋል።

በመረሀ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በአንድ ጀንበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል በአንድ መንፈስ አሻራን የማኖር ስራ የሚበረታታ፣ የሚስደስትና ወደፊትም መቀጠል ያለበት ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፤ የተተከሉ ችግኞችንም የመንከባከብ ስራ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡ የክልል የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከላትም በየአካባቢያቸው በመርሃግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።