የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በታለመው መሰረት ለመፈጸም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የኢትዮጵያን ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድን ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ግምገማና ውይይት በአዳማ ከተማ አድርጎል ።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሪማ የሱፍ መድረኩን ሲከፈቱት ባስተላለፋት መልዕክት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በታለመዉ መሰረት ለመፈፀም ሁሉም ፈጻሚ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል ።
የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅድ በየስራ ክፍሎቹ ኃላፊዎች ቀርቦ በተሳታፊዎች የቡድን ውይይትና ግምገማ ተደርጎበታል።
በዕቅድ ውይይቱ ማጠቃለያም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን በሚጠበቀው ልክ ለመፈጸም ተሳታፊዎቹ ቃል ገብተዋል። በመድረኩ መጨረሻም በኢትዮጵያ አስራሶስተኛ ወር የሆነችውን የጳጉሜ አምስት ቀናት አከባበርን በተመለከተ የተዘጋጀ ጹሑፍ በሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሂሩት አለሙ ቀረቦ ውይይት ተደርጎበታል ።