የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀንን አከበሩ

14 Oct, 2024 News

photo_2024-10-14_13-21-31

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀንን በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ቃለ መሃላ በመፈጸም ሰንደቅ ዓላማ የመስቀል ስነ- ስርዓት አከናውነዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ መሠረታዊ የሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት 17ኛው ብሔራዊ የሰንቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበር መሆኑን ጠቅሰው ሰንደቅ ዓላማችን የብሔራዊ አንድነታችንና የሉዓላዊነታችን መገለጫን መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር እንደአገርም ሆነ እንደሴክተር በተቋማችን ላይ የተጣለውን አደራና ኃላፊነት በመወጣት ቃል ኪዳናችንን በማደስ ሀገራችንና ህዝባችንን በትጋት የምናገለግልበት መሆን እንዳለበት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው አሳስበዋል፡፡

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተሻሻለው በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር መደንገጉ ይታወቃል፡፡