የጀርመን ልኡክ በኢንስቲትዩቱ ጉብኝት አደረጉ

24 Oct, 2024 News

germen

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ጀርመን ሀገር ከሚገኘው Institute of Meteorology and Climate Research (IMK-IFU) የተወጣጡ ፕሮፌሰሮች እና ተመራማሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድሚያ ማስጠንቀያ ም/ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ስለ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ስለሚሰጠው የአየር ሁኔታና ጠባይ ትንበያ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይታቸው ወቅትም ከ IMK-IFU ጋር በአቅም ግንባታ፤ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በሰው የሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)ዘዴን በመጠቀም የአየር ሁኔታና ጠባይ ትንበያ ለመስጠት በሚያስችል ስራዎች ላይ አብረው ለመስራት ውይይት አድርገዋል፡፡ ልኡኩ የኢንስቲትዩቱን የዳታ ማእከልና የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ክፍልን ጎብኝተዋል፡፡