የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያ አቅምን ለማጠናከር የሚያግዝ የ9.9 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘ

06 Nov, 2024 News

photo_2025-01-23_14-45-57

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተባበሩት መንግስታት ባለ ብዙ አጋር ፈንድ የሚደገፍ GBON-SOFF በሀገር ውስጥ የአየር ሁኔታ መከታተያ ጣቢያ በማቋቋም የምትሰበስባቸውና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ የምታጋራቸው የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ለማጠናከር የሚያግዝ ሲሆን ፕሮጀክቱ 9.9 ሚ. ዶላር በጀት ያለው ሲሆን በሶስት አመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው

የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ኢትዮጵያ እንደ ሁሉም 193 የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አባል ሀገራት ስምምነት መሰረት የአየር ሁኔታ መረጃን መሰብሰብ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተላለፍ ግዴታ ስላለባት ይህንን ግዴታዋን መወጣት እንድንችል የሚያግዛትን ይህንን ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረጓ መልካም እድል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ የSOFF-GBON ፕሮጀክት “ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም” ዓለም አቀፋዊ ተነሳሽነትን ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ከአደገኛ የአየር ሁኔታና ጠባይ እንዲሁም ከውሃ አደጋ ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡

በእለቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የUNDP የአገሪቷ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ሳሙኤል ዶይ፣ የሶፍ ፅ/ቤት ዳይሬክተር Mr. Markus Repnik እንዲሁም የአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅ/ቤት ዳይሬክተር ተወካይ የመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል፡፡