የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር አሶሴሽን የስራ አመራር ስብሰባውን እየካሄደ ነው

11 Aug, 2024 News

photo_2024-08-11_07-49-34

እ.አ.አ. ከኦገስት 9-10 ቀን 2024 በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ አህጉር አሶሴሽን የስራ አመራር ስብሰባ መድረክ በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር አሶሴሽን ፕሬዝዳንት እና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ በሆኑት በአቶ ፈጠነ ተሾመ እየተመራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመድረኩም 19ኛውን የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አሶሴሽን የመከረባቸውን እና ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠበቸውን ተግባራትና ከ2024-2027 በተለያዩ ኮሚቴዎች የሚተገበሩ ተግባራት አስመልክቶ አፈጸጸማቸውንና ዝግጅታቸው ገምግሟል፡፡

መድረኩ ከመጀመሩ በፊት ቀደም ተብሎ እ.አ.አ. ከኦገስት 6-9 ቀን 2024 ድረስ የተለያዩ ኮሚቴዎች ለስራ አመራሩ ቀርቦ ተገምግሟል ፡፡ የስራ አመራር ቦርዱ ከስብሰባው ጎን ለጎን በኪጋሊ የሚገኘውን የሩዋንዳ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ መሰረተ ልማት እና የአገልግሎት አሰጣጥን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።