News
የካሜሮን ልኡክ በኢንስቲትዩቱ

ከካሜሩን ከሚቲዎሮሎጂ ከግብርና እና ከአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር የተውጣጡ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ በመገኘት የስራ ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው። ስምንት አባላት ያሉት ይህ ልኡክን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በመቀበል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ በኢትዮጵያ ጥሩ ቆይታ እንዲኖራቸው ተመኝተዋል ቡድኑ ከነሐሴ 6 እሰከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የሚከናወኑትን ስራዎች በመከታተል የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ።