የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዪት ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደሩ የአየር ሁኔታና ጠባይ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዚዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ የሚሰጠውን የአየር ሁኔታና ጠባይ ትንበያ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገለጻ አድርገዋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) በአርብቶ እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚተገበረው ፕሮጀክት በአጠቃላይ 107 የሚደርሱ ዘመናዊ የሆኑ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያ በመትከል ተዓማኒነት ያለው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለመስራት ያግዛል ያሉ ሲሆን እንደሶማሌ ክልል ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው አካባቢዎች 38 የሚደርሱ ዘመናዊ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያዎች እንደሚተከሉ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በእለቱ የክልሉ የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ የሱፍ እንዲሁም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ወረዳ ተወካዮች ተገኝተዋል።