የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከአካባቢ ጥበቃና ከተባባሩት የዓለም መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በተመተባባር ያቋቋመው የሚቲዎሮሎጂ ጣቢያን አስመረቀ
ኢንስቲትዩቱ ከአካባቢ ጥበቃና ከተባባሩት የዓለም መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በተመተባባር በኦሮሚያ-ባቢሌ፣በማዕከላዊ ኢትዮጵያ-ዌራዲጆ፣ በሱማሌ-ሀረዋ እና በአፋር-ደዌ ላይ ሰው አልባ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያዎችን በማቋቋም ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አስተባባበሪ አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) በምረቃው ላይ እነዚህ ጣቢያዎች ቦታ ተኮር የአየር ሁኔታና ጠባይ ትንበያ ለመሰጠት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢንስቲትዩቱ የመሰረታዊ ሚቲዎሮሎጂ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያምም በምርቃው ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢንስቲትዩቱ ከ300 በላይ የሚሆኑ ዘመናዊ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያዎችን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመትከል መረጃ በመሰብሰብና በማደራጀት የተሻለ የአየር ሁኔታና ጠባይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡