የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከሞይንኮ ጋር የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለማሳለጥ የሚግዙ ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

09 Jan, 2025 News

photo_2025-01-09_14-50-40

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬከተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቀት እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በተፋሰስ ደረጃ ተዓማኒነት ያለው ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለመስራት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ከዓለም ባንክ ጋር የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ቀረጾ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ፕሮጀክቱ በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የሚቲዎሮሎጂ መረጃ መሰብሰቢያ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት የመስክ ተሸከርካሪዎች በጣም አስፈላጊ መሆናቸውንም ገልጻ አድረገዋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹን የሚያቀርበው ሞይንኮን በመወከል የአገር የችርቻሮ ሽያጭ አስተዳዳሪ አቶ አለኸኝ ገብሩ ሲሆኑ ፕሮጀክቱ የታለመለትን ዓላማ እንዲመታ ተቋማቸው ተሽከርካሪዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሰረከብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አስተባባሪና የትንበያ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ የሚገዙት ተሽከርካሪዎች ፕሮጀክቱ በሚከናወንባቸው የአዋሽ፤ የስምጥ ሸለቆ እና የኦሞ ተፋሰሶች ላይ ለሚተከሉት አንድ መቶ (100) ዘመናዊ የአየር ሁኔታ ጣቢያዎችን ለመትከልና ቦታ ተኮር የሆነ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን በፍጥነት ለማከናወን ያግዛሉ ብለዋል፡፡