News
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ጋር የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለትን በቅንጅት ለመተግበር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የተፈረመው ይህ ስምምነት በቆላማ አካባቢ ያለውን ዕምቅ አቅም እና ሃብት በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማምጣት በሚደረገው ስራ ውስጥ ኢንስቲትዩቱ ድርሻውን በሙሉ አቅሙ እንደሚወጣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ገልፀዋል።