የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ስራተኞች የኢንስቲትዩቱን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ግምገማ በማድረግ ውይይት አካሂደዋል

02 Jan, 2025 News

photo_2025-01-02_09-14-16

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ስራተኞች የኢንስቲትዩቱን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ግምገማ በማድረግ ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ የግምገማ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት እያከናወነ ላለው መጠነ ሰፊ የልማት ስራዎችን ለማገዝ ኢንስቲትዩቱ ከአጭር እስከ ረዥም ጊዜ ትንበያዎችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ሲያደርግ እንደነበር ጠቅሰው ለዚህ ተግባር አፈጻጸም ሰራተኛው ከፍተኛ ድርሻ አንደነበረው ገልፀዋል ።

የኢንስቲትዩቱን 2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የእቅድ የመደበኛ፣ የካፒታል እንዲሁም የለጋሽ አፈጻጸምን የሚመለከታቸው የስራ አስፈፃሚዎች በየስራ ዘርፉቸው ታቅደዉ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን አቅርበዋል።

ለተነሱ ጥየቄዎችና አስተያየቶች የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ፣ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሪማ የሱፍ እና የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ሙሉጌታ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሁም የቀጣይ የስራ ትኩረት አቅጣጫ በመስጠት ስብሰባው ተጠናቋል።