የኢትዮጵያን ልዕልና የሚያረጋግጥ እና ወደ ከፍታ የሚያሻግር ስራ መሰራት አንደሚገባ ተገለፀ

18 Nov, 2024 News

photo_2024-11-18_21-42-11

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንሰቲትዩት የዋናው መስሪያቤት እንዲሁም የም/መ ኦሮሚያ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከል አመራርና ሰራተኞች ገዥው ብልፅግና ፓርቲ የተመሰረተበትን 5ኛ ዓመት ''የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ቃል በድምቀት አክብረዋል

የኢንስቲትዩቱ  ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ  ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ  ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው የብልፅግና ፓርቲን የምስረታ በዓልን ስናከብር በተሰማራንበት የስራ መስክ የኢትዮጵያን ልዕልና የሚያረጋግጥ እና ወደ ከፍታ የሚያሻገር ስራ ለመስራት ቃል የምንገባበት እና የምንተጋበት መሆን ይገባዋል ብለዋል ።

በመረሀ -ግብሩ ላይ'የህልም ጉልበት፣ለምርታዊ ዕድገት'በሚል ርዕስ ለመንግሥት ሰራተኞች ግንዛቤ ማስጨበጫ የተዘጋጀ ሰነድ በኢንስቲትዩቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር በአቶክንፈ ኃ/ማሪያም ቀርቧል።

በመድረኩ ማጠቃለያም የኢንስቲትዩቱ ዋ/ዳ አቶ ፈጠነ ተሾመና ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም የቀረበውን ሰነድ ማዳበርና መግባባት የሚያስችል ውይይት ከተሳታፊዎችጋር አድርገዋል

በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ  እየተገነባ ያለውን አዲሱን ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት እና በአ.ሚ ድ የአፍሪካ አህጉር ጽ/ቤት መቀመጫ የግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል ጉብኝዎቹም በሰጡት አስተያየት እየተሰራ ያለውግንባታ እጅግ የሚያስደስትና ወቅቱንየዋጀ ህንፃ መሆኑን በመግለፅ መንግስት ለሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ከፍተኛ ትኩረት አድንቀውህንፃውንና ወቅቱን የሚመጥንአገልግሎት በመስጠት ብልፅግናን እንደሚያረጋግጡ ቃል ገብተዋል