የአየር ንብረት ለውጥ ዳሳሳ ጥናት ሪፖሪት ዝግጅት በቡልጋሪያ

61ኛው የዓለም በየነ መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል በቡልጋሪያ ሶፊያ ከተማ 7ኛውን የአየር ንብረት ለውጥ ዳሳሳ ጥናት ሪፖሪት ዝግጅትን አስመልክቶ እ.አ.አ ከጁላይ 27 ጀምሮ እስከ ኦገስት 2 ቀን 2024 ድረስ ተካሄደ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ፕሬዝዳንት እና በተባበሩት ዐረብ ኢሚሬትስ የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብደላ አልማንዱስ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል ፡፡ መደረኩም በአየር ጠባይ ለውጥ ሳይንስ፣ በአየር ጠባይ ተጋላጭነት ማቋቋሚያ እና ስርየት ዙሪያ እስከ 2029 ድረስ ለሚወጠው 7ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ዳሳሳ ጥናት ሪፖሪት የሚያግዝ ዝግጅት ዙሪያ መክሯል፡፡
ከዚህ መድረክ ጎን ለጎንም የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ፕሬዝዳንት እና በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብደላ አልማንዱስ እና የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ፈጠነ ተሾመ የቡልጋሪያ ሚቲዎሮሎጂና ሀይድሮሎጂ ኢንስትቲዩትን፣ በቡልጋሪያ የሶፊያ ዩንቨርስቲ አርክቲክ ሳይንስ ስልጠናና ምርምር ማዕከልን እና በሶፊያ በግል አጋርነት እየተከናወነ ያለውን የደመና ማበልጸጊያ ማዕከልን እና ግብኣትን በመጎብኘት የልምድ ለውውጥና ተሞክሮ ወስደዋል፡፡