የአየር ትንበያ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እየሰጠ መሆኑ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፁ

25 Jan, 2024 News

DG

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ጥር 03/2016 ዓ.ም ከሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአየር ትንበያ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን እየሰጠ መሆኑን ገልፀው ባለፈው የበጋ ወቅት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደተስተዋለባቸውና ይህም ሁኔታ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ለሚገኙ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑ አብራርተዋል።

በሰሜን አጋማሽ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የነበረው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ስብሰባ ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ ማድረሱን ገልጸዋል።

ዋና ዳሬክተሩ ለመጭው የበልግ 2016 ዓ.ም ትንበያ በኢሊኖና ላሊና ተፅዕኖ ውስጥ የሚቆይ እንደሆነ ገልፀው የበልግ ወቅት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

የወቅቱ ዝናብ አጀማመር በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቀድሞ እንደሚጀምርና በአወጣጥ ረገድ ግን ሊዘገይ እንደሚችልና በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛው አንፃራዊ እንደሚጨምር ገልፀዋል።

Tags: የበልግ 2016 , ጥር 03/2016 ዓ.ም