የበልግ ወቅት ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል

25 Jan, 2024 News

Tercile probability belg 2024

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጥር 3 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ያለፈው የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና በሚቀጥለው የበልግ ወቅት የሚጠበቀውን የወቅት አየር ጠባይ አዝማሚያን ይፋ ለማድረግ ባዘጋጀው መድረክ ላይ መጪው በልግ አሁን በትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ በላይ መሞቅ (ENSO-EL NINO) እንዲሁም የሰሜናዊ ህንድ

ውቅያኖስ መደበኛ የባህር ወለል ሙቀት መጠን (Neutral IOD) ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል የትንበያ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ተገልጿል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የወቅቱ

ዝናብ አጀማመር በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቀድሞ እንደሚጀምርና በአወጣጥ ረገድ ግን ሊዘገይ እንደሚችል እንዲሁም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው ለሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸው ታውቋል።

Tags: በልግ 2016 , Neutral IOD