የቆላማ አካባቢን ኑሮን መቋቋም የሚያስችል ፕሮጀክት- በአፋር

21 Nov, 2024 News

photo_2024-11-21_14-31-00

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለአርብቶ አደርና ለከፊል አርብቶ አደሩ የአየር ሁኔታና ጠባይ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ ፕሮጀክት በአፋር ክልል ይፋ አደረገ

የኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ኢንስቲትዩቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት የገለፁ ሲሆን በአርብቶና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት 107 የሚደርሱ ዘመናዊ የሆኑ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያና በመትከል ተዓማኒነት ያለው ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለመስራት ያግዛል ብለዋል፡፡ በአፋር ክልል ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው አካባቢዎች 23 የሚደርሱ ዘመናዊ የአየር ሁኔታ መመዝገቢያ ጣቢያዎች እንደሚተከሉ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የቆላማ አካባቢን ኑሮን የሚያሻሽል ይህ ፕሮጀክት በአገሪቱ ሰባት ክልሎችና አንድ የከተማ መስተዳድርን የሚሸፍን መሆኑን ከፕሮጀክት አስተባባሪው ማወቅ ተችሏል፡፡