የመኮ ራዳር ማቋቋሚያ ሳይት ዙሪያ ከባለድርሻዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

21 Dec, 2024 News

photo_2024-12-21_12-23-36

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ከፊላንድ መንግስት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን አቅም ለመገንባት ባደረገው የብድርና እርዳታ ስምምነት ከሚተከሉት ሶስት ራዳሮች ውስጥ የመኮ ሳይት ለሚገኙ የወረዳው የህ/ተ/ም/ቤት አባል፣ ከቡኖ በደሌ ዞን አስተዳደር እና የመኮ ወረዳ አስተዳደር እንዲሁም የተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የወረዳው ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ

ውይይቱን የመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ በመኮ ወረዳ የሚተከለው የአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር በ250ኪ.ሜ. ራዲየስ በከባቢ አየር ውስጥየሚከሰቱ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶችን መረጃ የሚሰበስብ በተለይ አስጊ የአየር ሁኔታ መረጃን በመጠቀም እንደ ቅጽበታዊ ጎርፍ፣ ከፍተኛ ንፋስና መሰል ክስተቶችመረጃን ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ተግባርለማዋል የሚያስችል መሆኑን ገልፀው በፌደራል መንግስት ድጋፍ የሚቋቋመውይህ ጣቢያ በፍጥነትና በጥራትለመስራት የዞንናየወረዳ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእለቱ የምእራብ ኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከል-ጅማ- ስራ አስፈፃሚ አቶ ገመቹ ራጋ ማእከሉ ስለሚሰጠው አጠቃላይአገልግሎት፣ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ በአቶ ሄኖክ ኃይሉ ስለፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በአቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም ራዳሩ የሚቋቋምበት ቦታትልልቅ ኮንቴነር የጫኑ ከባድ ተሸከርካሪዎችን ወደ ራዳር መትከያ ቦታ ለማድረስ የሚያስፈልገውን የመዳረሻ መንገድ ጥገና አስፈላጊነት እና የዞንና የወረዳ አመራሮችና ሊያደርጉ ስለሚገባው ድጋፍ ገለፃ አድርገው ሰፊ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ በመድረስ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል