የህንድ ተወካዮች በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አደረጉ
ከህንድ የተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ የቢሮ ሃላፊዎች፣ ፕሮፌሰሮችና ሳይንቲስቶች ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢንስቲትዩቱ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ የእንኳን ደህና መጣችው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሳምነው ተሾመ አጠር ያለ ገለፃ አድረገው ሰፊ ውይይት አድረገዋል፡፡ ልኡኩም ባዩት ነገር እጅግ መደሰታቸውንና በቀጣይም በአቅም ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡