ኢንስቲትዩቱ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የስራ ክፍሎች ስልጠና ተሰጠ

24 Oct, 2024 News

photo_2023-11-12_07-04-36

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከልደታ ክ/ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከታተልና መቆጣጠር እና ከልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ጋር በመተባበር 87 ለሚሆኑ የጽዳት፣የጥበቃና ሁለገብ ሰራተኞች መሠረታዊ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም መሠረታዊ የጥበቃ ሂደት፣ የጥበቃ ስነ ምግባር፣ የመሳሪያ አጠቃቀም፣ የሚፈነዱና ተቀጣጣይ መሳሪያዎች አይነትና ቢያጋጥሙ ሊወሰዱ ስለሚገቡ እርምጃዎችና የፍተሻ ስርዓትና ከፍተሻ ጋር ተያይዞ ሊወሰዱ ስለሚገባ ጥንቃቄና ሀላፊነቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ከጽንሰ ሀሳብ በዘለለ በተግባር የተደገፈ ሲሆን ለስምንት ተከታታይ ቀናት እንደቆየ ታውቋል፡፡