አዲስ አበባ ከጠበቅነው በላይ ተለውጣለች

22 Jan, 2025 News

photo_2025-01-23_15-36-47

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የአየር ጠባይ ትንበያ ማእከል ያዘጋጀውን 69ኛውን የቀጠናውን የአየር ጠባይ ትንበያ ፎረምን ለመካፈል የመጡ የአባል አገራት የሚቲዎሮሎጂ ተቋም ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሚዲያዎች በለውጥ ጎዳና ላይ ያለችውን አዲስ አበባን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸውም ስለ አዲስ አበባ ከሰሙት፣ ካዩትና ከጠበቁት በላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከከተማው እድገት በተጨማሪ የኢትዮጵያዊያኖች እውነት እንዲሁም የአፍሪካዊያኖች ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን መጎብኘታቸውና ታሪኩን በአግባቡ መስማታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለፅ ጉብኝቱን ያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን አመስግነዋል፡፡