በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ላይ መደበኛ እና ከመደበኛ በታች ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቆመ


የበጋ 2017 ወቅት በትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ በታች መቀዝቀዝ (ENSO-LA NINA) ሲሆን እንዲሁም የሰሜናዊ ህንድ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ (IOD- NEUTRAL) ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል የተተነበየ ሲሆን ከዚሁ ጋር
በተያያዘ የወቅቱ ዝናብ አጀማመር በደቡብ አጋማሽ አካባቢዎች ላይ መደበኛ ፈሩን ተከትሎ የሚጀምር ሲሆን በአወጣጥ ረገድ ግን ቀድሞ ሊወጣ እንደሚችል ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የበጋ ወቅት ትንበያን ይፋ ባደረገበት በዚህ መድረክ በአጠቃላይ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የቦረናና ጉጂ ዞኖች፤ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ መደበኛ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን፤ የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል ደግሞ ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚያገኙ በትንበያው የተመላከተ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማደረግ እንደሚገባው ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።