በጂቡቲ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ

20 Nov, 2024 News

photo_2024-11-20_08-45-16

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ የልዑካን ቡድኑን ተቀበለው ያነጋገሩ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ በተለይም በትንበያ ዘረፍ ተዓማኒነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለመገንባት በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ኢንስቲትዩቱ በትንበያ ዙሪያ ለምስራቅ አፍሪካ የሚቲዎሮሎጂ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና ለጂቡቲና ለሌሎች ሀገሮች የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች ላይ ልምዱንና የሀገራቱን አቅም ለመገንባት ቃል የገቡ ሲሆን እንደ አፍሪካ ፕሬዝዳንትነትም የአህጉሩ አቅም እንዲገነባ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ የጂቡቲ ልዑካን ቡድንም ከኢንስቲትዩቱ ልምድ ለመውሰድና በቀጣይም አብሮ ለመስራት ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት ገልፀዋል፡፡ ለልዑካን ቡድኑ ለስምንት ቀናት በኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች በትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ላይ ስልጠና ይሰጣቸዋል፡፡