በደቡብ ክልልየቆላማ አካባቢን ኑሮንለመቋቋም የቅድመማስጠንቀቂያ ስርዓትንለመዘርጋት የሚያግዝ ፕሮጀክትይፋ ሆነ

28 Dec, 2024 News

photo_2024-12-28_16-27-57

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትየቆላማ አካባቢንኑሮን ለመቋቋምየቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችንናስርዓትን በወረዳደረጃ ለመዘርጋትየሚያግዝ ከመስኖና ቆላማአካባቢ ልማትሚኒስቴር ጋርበመሆን እየተገበረ ያለውፕሮጀክት በደቡብኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማይፋ አደረገ

የኢንስቲትዩቱ ዋናዳይሬክተርና በአለምየሚቲዎሮሎጂ ድርጅትየአፍሪካ አህጉርፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ መድረኩንበንግግርበከፈቱበት ወቅትየጣቢያ ተደራሽነትን ለማሳደግናየትንበያናቅድመ ማስጠንቀቂያስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከርከመንግስት ከሚመደብለትበጀት በተጨማሪከባለድርሻ አካላት ወይምአጋር ድርጅቶችጋር መስራትወሳኝ በመሆኑ ከመስኖናቆላማ አካባቢልማት ሚኒስቴርጋርም እየሰራ ያለውይህ ፕሮጀክትምአንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውምከቅርብ ጊዜወዲህ የተፈጥሮ አደጋዎችበአገራችን እየተከሰቱ መሆናቸውበማስታወስ የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችንመጠቀምህይወትናንብረት ከአደጋለመከላከል አስፈላጊመሆኑን ገልፀዋል

በእለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ያስተላለፉትበደቡብ ኢትዮጵያክልል የአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢጉዳዮች ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ አይዴ ሎሞዶ የሚቲዎሮሎጂመረጃና ቅድመማስጠንቀቂያለክልላችን እጅግወሳኝ በመሆኑ በየወረዳዎቹለሚቋቋሙትየቅድመ ማስጠንቀቂያስርዓቶችና ለሚተከሉት የአየርሁኔታ መመዝገቢያጣቢያዎችየየወረዳዎቹ ኃላፊዎችከፍተኛ ትኩረትበመስጠት ውጤታማእንዲሆኑ አሳስበዋል

በደቡብ ክልልተግባራዊየሚደረገው ይህፕሮጀክት በ7 ወረዳዎችማለትም ሃመር፣ዳሰነች፣ኛንጋቶም ቤናፀማይ፣ማሌ፣ ሰልማንጎና ኮላንጎ ላይየሚተገበርሲሆን የየወረዳዎቹአስተዳደር፣የግብርናየእንስሳት ሀብትልማት፣የውሃ፣የጤና፣የአደጋስጋት እንዲሁም ቆላማአካባቢ ቢሮሃላፊዎችናባለሙያዎች በመድረኩላይ ተገኝተዋል