በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ጉብኝት ያደረጉት የቻይና ሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር ልኡክ በቆይታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገለፁ

02 Dec, 2024 News

photo_2024-12-02_17-07-43

የቻይና ሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር አስተዳዳሪ እና በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የቻይና ቋሚ ተጠሪ በሆኑት በDr. CHEN Zhenlin የተመራው ልኡክ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ልኡኩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የሚቲዎሮሎጂን የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅምን በማሳደግ ዙሪያ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በሁለቱም ወገን በተደረገው የጋራ ስምምነት ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚቲዎሮሎጂ፣ በአየር ጠባይ ትንበያ፣ በአየር ንብረት መከታተያ ራዳር፣ ሰው ሰራሽ ዝናብ ማሻሻል፣ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና የመሳሰሉት የያዘ ነው፡፡ ይህ የጋራ ስምምነት ለቀጣይ አምስት አመት

(2025-2029) ተግባራዊ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡

በተያያዘም የቻይና ሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር ልኡክ በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፅ/ቤትን፣ ኢንስቲትዩቱ እያስገነባ ያለውን የቦሌ ህንፃ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩትንና እንጦጦ ኦብዘርቫቶሪን እንዲሁም በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምስራቅና መካከለኛው ኦሮሚያ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማእከልን -አዳማ ጎብኝተው ለሶስት ቀን የነበራቸውን የኢትዮጵያ ቆይታ አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡