በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቆላማ አካባቢን ኑሮን ለመቋቋም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የቆላማ አካባቢን ኑሮን ለመቋቋም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችንና ስርዓትን በወረዳ ደረጃ ለመዘርጋት የሚያግዝ ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተገበረ ያለው ፕሮጀክት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ ይፋ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የትንበያና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አስተባበሪ ዶክተር አሳምነው ተሾመ መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ኢንስቲትዩቱ የጣቢያ ተደራሽነትን ለማሳደግና የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበትና በቅንጅት መስራት ወሳኝ በመሆኑ ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር ጋርም እየሰራ ያለው ይህ ፕሮጀክትም አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡