በሚቲዎሮሎጂ ዘርፍ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸዉ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረ የሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ ተመራማሪዎች ፎረም ተጠናቀቀ።
በፎረሙ ላይ ከአስራ አንዱም የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የተወጣጡ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በዘርፉ የተደረጉ የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ስራዎች ቀርበው የጥናት ሰነዶቹን ማዳበር የሚያስችል ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጓል።
ከጥናት ሰነዶች በተጨማሪ የሰው ሰራሽ አስተውሎ (AI) ለሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት የሚኖረው ሚና እንዲሁም የሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ ተመራማሪዎች የኬሪየር አፈጻጸም መመሪያም ቀርቦ ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቶል።
በፎረሙ ላይ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በሰጡት አስተያየት የቀረቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለቀጣይ ስራቸው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው በሚቲዎሮሎጂ ሳይንስ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።