ቋሚ ኮሚቴው የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴን ጎበኘ

29 Jan, 2024 News

Standing committee

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ መስኖና ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የእንጦጦ ጣቢያ እና አዲስ እያስገነባ ያለውን የቦሌ ህንፃ ግንባታ ጉብኝት አድርገው ስራው ያለበትን ደረጃ ገምግመዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲያ አህመድ የጉብኝታቸው አጠቃላይ ግምገማ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ በአጠቃላይ በጣም ጥሩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በህንፃው ግንባታ ላይ እየታየ ያለውን መዘግየት ክትትል እንደሚያስፈልገው አሳስበዋል፡፡