ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች ለሁሉም “Early warnings for all (EW4All) ፕሮግራም ላይ ብሔራዊ የባለድርሻ አካላት የምክክር አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም/UNDP/ በጋራ ያዘጋጁት የምክክር አውደ ጥናት ለሁለት ቀን የሚቆይ ሲሆን ቅድመ ማስጠንቀቂያዎች ለሁሉም “Early warnings for all (EW4All) ፕሮግራም ላይ ብሔራዊ የባለድርሻ አካላት ክፍተቶችን ለመለየትና በፕሮግራሙ ዋና ምሰሶዎች ላይ ውይይት ለማድረግ ነው፡፡