ሶፍ በጋምቤላ

05 Jan, 2025 News

photo_2025-01-05_03-28-51

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሀገር ውስጥ የአየር ሁኔታ መከታተያ ጣቢያ በማቋቋም የምትሰበስባቸውና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ የምታጋራቸው የሚቲዎሮሎጂ መረጃዎችን ለማጠናከር የሚያግዘ ፕሮጀክት በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርና በአለም የሚቲዎሮለጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ ኢንስቲትዩቱ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ በጋምቤላ ክልል የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊረባረቡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በእለቱም ጉዳዮ የሚመለከታቸው የክልሉ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡