መጪው የበልግ ወቅት አሁን በትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ እንደሚሆን ተገልጸ

26 Jan, 2025 News

photo_2025-02-14_12-58-29

መጪው በልግ አሁን በትሮፒካል ፓስፊክ ውቅያኖስ የባህር ወለል ሙቀት ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ (ENSO-Neutral) እንደሚሆን እንዲሁም የሰሜናዊ ህንድ ውቅያኖስ መደበኛ የባህር ወለል ሙቀት መጠን (Neutral-IOD) ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል ያለፈው የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና በሚቀጥለው የበልግ ወቅት በሚጠበቀው የወቅት አየር ጠባይ አዝማሚያን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገልጿል፡

የወቅቱ ዝናብ አጀማመር በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ቀድሞ እንደሚጀምርና በአወጣጥ ረገድ ግን ሊዘገይ እንደሚችል እንዲሁም ተደጋጋሚነት ያለው ደረቅ ሰሞናት እንደሚኖሩ የተተነበየ ሲሆን ህብረተሰቡም በሚቀጥለው የበልግ ወቅት የሚጠበቀውን የአየር ጠባይ ትንበያን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባትና የሚገኘውን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ በመጠቀም በዚህ ወቅት የሚካሄደውን የግብርና እንቅስቃሴና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎችን ከባለሙያዎች ጋር በመመካከር ማከናወን እንዳለበት እንዲሁም ዝናብ አጠር በሆኑት አካባቢዎች በየዕለቱ የሚኖረውን የዝናብ መጠንና ስርጭት በአግባቡ በመሰብሰብ መጠቀም እንደሚገባ ተጠቁሟል፡

በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት ተደጋጋሚነት ያለው ከባድ ዝናብ የሚኖር መሆኑንና ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑት ረባዳማና የወንዝ ዳርና በከተሞች አካባቢዎች የማህበራዊና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሥራዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ እንዲያስችል አስፈላጊውን የጥንቃቄ ስራ ከወዲሁ መከናወን እንዳለበት ለሚመለከታቸው አካላት ምክረ ሃሳብ ቀርቧል