ለሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከላት ተመራማሪዎች ከወቅት አጋማሽ እስከ ወቅት ድረስ ትንበያን ለማሻሻል በሚያግዙ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘዴ ላይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

11 Oct, 2024 News

photo_2024-10-11_12-13-49

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና በዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት አቶ ፈጠነ ተሾመ የስልጠና መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ በሀገር አቀፍ ደረጃና በክልል በሚሰጡ የአየር ሁኔታ ትንበያና ምክረ ሀሳቦችን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግና ተዓማኒነቱን ለመጨመር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ማብራሪያ ሰተዋል፡፡ በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ ከምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት የአየር ጠባይ ትንበያ ማዕከል ጋር በመተባበር ባገኘው ፕሮጀክት የተመራማሪዎችን አቅም ለማሳደግ እና የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስራዎችን ለማጠናከር ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ያሉት ደግሞ በኢንስቲትዩቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አሳምነው ተሾመ ገለጻ አድረገዋል፡፡