Bega 2026/27 Seasonal Climate Forecast

Bulletin

በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በጉጂ፤ በቦረና፤ በሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች፤ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፤ የምዕራብና የደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ከመደበኛዉ በላይ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በሰሜን፤ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡